1. ኢየሱስ አገልግሎቱን ሲጀምር እድሜው ስንት ነበር?
2. የኢየሱስ ሐዋርያት ስንት ነበሩ?
3. የጳውሎስ የመጀመሪያው ስሙ ማን ነበር?
4. አራቱ ወንጌላት በመጽሐፍ ቅዱስ አቀማመጥ መሰረት ሲደረደሩ እንዴት ነው?
5. "በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።" የሚለው ጥቅስ ያለበት ምዕራፍ የትኛው ነው?
6. ዮሐንስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስንት መጽሐፎችን ጽፏል?
7. ኢየሱስ የነጎድጓድ ልጆች ብሎ የጠራቸው እነማንን ነው?
8. አብርሃም ልጁ ይስሐቅ ሲወለድለት ዕድሜው ስንት ነበር?
9. ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በጌቴሴማኒ ያላቸው ምንድን ነው ተኝተው ሲያገኛቸው?
10. "እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ" ብሎ የፀለየው ማን ነው?